የአማኞች እናት፣ የዐብደላህ እናት ከሆነችው ከዐኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በዚህ ጉዳያችን ከእርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር ያመጣ ይዞት የመጣው አዲስ ፈሊጥ ውድቅ ነው።"» በሌላ የሙስሊም ዘገባም "በርሱ ላይ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ነገር የሰራ ሰዉ ስራው ወደርሱ ተመላሽ ነዉ።" ሶሒሕ ነው። - رواه البخاري ومسلم