ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - “አዎን!” አሉት።» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።
explain-icon

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።

explain-icon

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  • አንድ ሙስሊም መጨረሻው ጀነት መግባት እንዲሆን፥ ግዴታዎችን በመተግበር እና ክልከላን በመተው ላይ ጥረት ሊኖረው ይገባል ።
  • ሐላል ፍቁድ ነገሮችን ፍቁድነታቸውን በማመን መተግበርና ክልክል ነገሮችን ክልክልነታቸውን በማመን መራቅ አሳሳቢ (ወሳኝ) ጉዳይ መሆኑን ፤
  • ግዴታዎችን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ጀነት መግቢያ (ሰበብ) ምክንያት ነው።