ከአማኞች እናት ከዓኢሻህ (ረዲየሏሁ ዓንሃ) -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሩብ ዲናርና ከዛ በላይ በሚያወጣ (ስርቆት) እጅ ይቆረጣል።"» ሶሒሕ ነው። - ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።