ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ከስሞቻችሁ መካከል አላህ ዘንድ ተወዳጁ ስም ዐብዱላህና ዐብዱረሕማን ናቸው።"» ሶሒሕ ነው። - ሙስሊም ዘግበውታል።