ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ: "ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"» ሶሒሕ ነው። - አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።