ከአቢ ጀዕድ አድዶምሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - (ከነቢዩ ሶሓቦች መካከልም አንዱ ነበር) እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።" ሶሒሕ ነው። - رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه وأحمد